ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ለኢትዮጵያ ለሚያደርገው ድጋፍ ምስጋና አቀረቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ቢል ጌትስ ከ2010 ዓመተ ምህረት በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ እንኳን ወደ ምድረ ቀደምት ኢትዮጵያ መጡ እላለሁ ብለዋል።

ቢል እና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በግብርና፣ በጤና እና የፋይናንስ ዘርፉን አካታች ለማድረግ በሚደረጉ ጥረቶች ለሚያደርግልን ያልተቋረጠ ድጋፍ በጣም እናመሰግናለን ሲሉ ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዛሬው በስንዴ ክለስተር ልማት እና የዶሮ እርባታ ላይ ያተኮረ ጉብኝት ኢትዮጵያ በምግብ ራስን በመቻል ጥረት መንገዷን አጽንታ ባለበት ወቅት የተጠናከረውን ትብብራችንን የበለጠ የሚያጠናክር ነው ብለዋል በመልዕክታቸው።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ነሐሴ 27 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *