ከተላኩ 95 የሚሆኑ የዘረመል ምርመራ ይደረግልኝ ጥያቄዎች ውስጥ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድቤት የህፃናት ፍትህ ፕሮጀክት ድጋፍ 71 ለሚሆኑት ምርመራው እንደተደረገ አስታውቋል፡፡
የፕሮጀክቱ ዳይሬክተር ዳኛ ተክለ ሀይማኖት ዳኜ ከጣቢያችን ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት ምርመራ ከተደረገባቸዉ 71 ጉዳዮች ዉስጥ 7ቱ በስምምነት ልጆቹ አባትነታቸዉን እንዲያዉቁ ሲደረግ 52 ቱ በምርመራዉ የልጆቹ አባት መሆናቸው ተረጋግጧል ብለዋል፡፡
ቀሪዎቹ 6ቱ ደግሞ በተደረገው የዘረመል ምርመራ አባት አለመሆናቸው ተረጋግጧል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ሌሎች የቀረቡ ስድስት ጥያቄዎች ምርመራ ተደርጎላቸዉ ዉጤታቸዉን እየተጠባበቁ እንደሚገኙም አንስተዋል ፡፡
የበጀት እጥረት ትልቅ ፈተና እንደሆነ ያነሱት የፕሮጀክቱ ዳይሬክተር በአመቱ ለዘረመል ምርመራ ከ1.5 እስከ 2 ሚሊዬን ብር የሚደርስ ወጪ መደረጉን ጠቅሰዋል ፡፡
ፕሮጀክቱ በህግ ስርአቱ በተከራካሪነት እና በተከሳሽነት አንዲሁም በተጠቂነት የሚያልፉ ህፃናትን ለመደገፍ የተቆቆመ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
አቤል እስጢፋኖስ
ነሐሴ 30 ቀን 2016 ዓ.ም
