በበሽታው እስካሁን የ8 ሰዎች ህይወት ማለፉን የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ አስታውቋል ።
የቢሮው የማህበረሰብ ተሳትፎ እና ጤና ክብካቤ ዋና ባለሙያ የሆኑት አቶ ሙላት ታደሰ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት 341የሚሆኑት በቂ የሆነ ህክምና አግኝተው ወደ ቤታቸው መሄዳቸውን ተናግረዋል ።
አሁን የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው የሚገኙ ሰዎች ቁጥረረ 31 እንደሆነ አንስተዋል ።
በሽታው በትግራይ ክልል በ27 ወረዳዎች መታየቱንም ጠቅሰዋል ።
ስርጭቱ በአብዛኛው እየታየ ያለው ሰሜን ምዕራብ ዞን፤ አስገደ ወረዳ መሆኑንም ገልፀዋል።
በዚህ በሽታ በብዛት እየተጠቁ የሚገኙት በወርቅ ማውጣት ስራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ናቸው ብለዋል ።
ህክምናውን ለማድረግ የሚረዱ የግብአት እና የበጀት እጥረቶች መኖራቸውንም አንስተዋል።
ችግሩን ለመቅረፍ በተቻለ መጠን ወደ ሌሎች ወረዳዎች እንዳይስፋፋ እና ባለበት አካባቢ የመቆጣጠር ስራዎች እየሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል ።
በሽታው ከዚህ በላይ እንዳይስፋፋ እና ጉዳት እዳያስከትል የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ቢያደርጉ የሚል መልዕክታቸውንም አስተላልፈዋል።
ሐመረ ፍሬው
ነሐሴ 30 ቀን 2016 ዓ.ም
