ከ200ሺህ በላይ ዜጎች የሚሳተፉበት “ኢሬቻ ኤክስፖ 2017” የተሰኘውን ታላቅ ዐውደ ርዕይ ተዘጋጀ

ሀገሬ ኢቨንትስና ፕሮሞሽን  ከኦሮሚያ ባህልና ቱሪዚም ቢሮ ጋር በመተባበር በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን “የኢሬቻ ኤክስፖ 2017” የተሰኘውን ታላቅ ዐውደ ርዕይ ሊያዘጋጁ ነው ።

“ኢሬቻ ኤግዚቢሽንና ባዛር 2017 የተለያዩ የሕብረተሰብ ከፍሎችን የሚያሳትፍ፣ እንዲሁም ከውጭ አገር ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ታዳሚ የሚሆኑበት ነው ተብሏል።

የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዚም ቢሮ ም/ሃላፊ አቶ ዳሬሳ  ከተማ እንዳሉት ይህ የኢሬቻ ኤግዚቢሽንና ባዛር 2017 የሚቆየው ከመስከረም 18 እስከ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ነው።

አቶ ዳሬሳ የዘንድሮው ኤግዚቢሽንና ባዛር የኦሮሞ ሕዝብና ወንድም ኢትዮጵያዊያን ባሕላዊ ትሩፋቱን የሚከብር ብቻ ሳይሆን በዓሉን አስመልክቶ ማህበረሰቡን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ  የሚያደርግ ነው ብለዋል።

የሀገሬ ኢቨንትስና ፕሮሞሽን ዋና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ  ሃወኔ ኢሼቱ  በበኩላ በተዘጋጀው የንግድ ኤግዚቢሽ የባሕል አልባሳትና ጌጣጌጥ አምራችና ነጋዴዎች፣ ባንኮች፣ የፈጠራ ባለሙያዎችና ሥራ ፈጣሪዎች፣ የሪል እስቴት አልሚዎችና ሌሎች የተለያዩ ከ250 በላይ ተቋማት ምርትና አገልግልቶቻቸውን የሚያቀርቡበትም ጭምር ነው ብለዋል ።

“ኢሬቻ ኤግዚቢሽን እና ባዛር 2017″  ላይ ከፍተኛ የፌዴራልና የክልል የመንግሥታት ባለሥልጣናት፣ ታዋቂ ሰዎች፣ ምሑራን እና ተመራማሪዎች አባ ገዳዎችና ሐዳ ሲንቄዎች ይገኙበታል ተብሏል ።

በዘንድሮ አመት የኢሬቻ ክብረ በዓል ላይ ከ10 ሚሊየን በላይ ዜጎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ።

ልዑል ወልዴ

መስከረም 8 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *