የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ የማጣርያ ከጊኒ ጋር የሚያደርጋቸውን ሦስተኛ እና አራተኛ የምድብ ጨዋታዎች ላይ የቀን እና የቦታ ለውጥ ተደርጓል።
የኢትዮጵያ እና የጊኒ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ለካፍ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት በጨዋታዎቹ ላይ የቦታ እና የቀን ሽግሽግ የተደረገበት ሲሆን ሦስተኛው የምድብ ጨዋታ ጊኒ የሜዳዋ ጨዋታን ለማድረግ ያስመዘገበችው ያሞሱክሩ የሚገኘው ስታድ ኮናን ባኒ ወደ አቢጃኑ ስታድ ደ ኢቢምፔ ፤ የጨዋታው ቀን ደግሞ በአንድ ቀን ተራዝሞ ጥቅምት 2/2017 ከምሽቱ 1፡00 ላይ የሚያከናውን ሲሆን አራተኛ የምድብ ጨዋታውን በተመሳሳይ ከጊኒ ጋር ጥቅምት 4 ሊደረግ የነበረው ጨዋታ በአንድ ቀን ተራዝሞ ወደ ጥቅምት 5/2017 ተሸጋሽጓል። የቦታ እና የሰዓት ለውጥ ሳይደረግበትም አቢጃን የሚገኘው ስታድ ደ ኢቢምፔ ምሸት 4፡00 ላይ ያከናውናል።
በጋዲሳ መገርሳ
መስከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም
