የ 2024 የቻን አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ድልድል በግብፅ ካይሮ ተካሂዷል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ” ዋልያዎቹ ” በማጣሪያው በመጀመሪያው ዙር ከኤርትራ ብሔራዊ ቡድን ጋር ተደልድለዋል።
- የመጀመሪያው ዙር :- ኢትዮጵያ ከ ኤርትራ
- ሁለተኛው ዙር :- ኢትዮጵያ / ኤርትራ ከ ታንዛኒያ / ሱዳን
የመጀመሪያ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታ ከጥቅምት 15-17 ባሉት ቀናት እንዲሁም የመልስ ጨዋታዎች ከጥቅምት 22-24/2017 ባሉት ቀናት ይደረጋል።
የሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታ ከ ታህሳስ 11 – 13 እንዲሁም የመልስ ጨዋታዎች ከታህሳስ 18-20/2017 ባሉት ቀናት ይካሄዳል ።
የ 2024 የአፍሪካ ሀገራት ሻምፒዮን ሽፕ ( ቻን ) ውድድር ከጥር 24 እስከ የካቲት 21/2017 ዓ.ም ይካሄዳል።
የዘንድሮው የቻን ውድድር በኬንያ ፣ ዩጋንዳ እና ታንዛኒያ አዘጋጅነት በአስራ ዘጠኝ ክለቦች መካከል የሚካሄድ ይሆናል።
በጋዲሳ መገርሳ
መስከረም 29 ቀን 2017 ዓ.ም
