ሰሜን ኮሪያ ከደቡብ ኮሪያ ጋር የሚያገናኟትን የመኪና እና የባቡር መስመሮችን በማቋረጥ ሁለቱን አገራት “ሙሉ በሙሉ ለመለያየት” መወሰኗን ገለጸች።

“ደቡባዊው ድንበር በዘላቂነት ይዘጋል” ያለው የአገሪቱ ጦር፤ በራሱ ድንበር በኩል ያሉ ቦታዎችን ጥበቃ እንደሚያጠናክር አስታውቋል።

በደቡብ ኮሪያ ውስጥ የሚደረጉ የጦርነት ልምምዶች እና የአሜሪካ የኒውክሌር ንብረቶች በአከባቢው በተደጋጋሚ መገኘታቸውን በመግለጽ እርምጃውን “ጦርነትን

ለመግታት ራስን የመከላከል እርምጃ” ሲል የኮሪያ ህዝብ ጦር (ኬፒኤ) ገልጾታል።
ውሳኔው በኮሪያ መካከል ያለው ውጥረት ከዓመታት በኋላ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በደረሰበት በዚህ ወቅት ያለውን ፍጥጫ መባባሱን ያሳያል።

“በኮሪያ ግዛት ላይ ያለው አስቸኳይ ወታደራዊ ሁኔታ ከግምት በማስገባት የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮሪያ ኃይሎች የአገሪቱን ብሔራዊ ደኅንነትን በብቃት ለመጠበቅ የበለጠ ቆራጥ እና ጠንካራ እርምጃ እንዲወስዱ ይጠይቃል” ሲል ኬፒኤ በመንግስታዊው መገናኛ ብዙሃን ኬሲኤንኤ በኩል አስታውቋል።

መግለጫው በአብዛኛው የፒዮንግያንግ የይስሙላ እርምጃ ነው።
ቀደም ብሎም ቢሆን ከሰሜን ኮሪያ ወደ ደቡብ የሚወስዱ መንገዶች እና የባቡር ሃዲዶች እምብዛም ጥቅም ላይ አይውሉም።

መስመሮቹም በሰሜን ኮሪያ ባለስልጣናት ባለፈው ዓመት ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲፈርሱ ተደርገዋል።

ውሳኔው ከደቡብ ኮሪያ ጋር ያላትን ግንኙነት እንድትቀይር በፒዮንግያንግ ላይ ሰፊ ግፊት በጨመረበት እና በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ያበላሹ በርካታ ቀስቃሽ ክስተቶችን ተከትሎ የመጣ ነው።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *