የኬንያው የስልክ ኔትዎርክ ኦፕሬተር የሆነው ሳፋሪኮም በ ‘ኤም-ፔሳ ግሎባል’ በተሰኘው አገልግሎቱ ኢትዮጵያን ማካተቱ ተገልጿል።
ይህም ደንበኞች ከኬንያ ወደ ኢትዮጵያ የሞባይል ገንዘብ ልውውጥ እንዲያደርጉ የሚያስችላቸው ነው ተብሏል።
በኬንያ ያሉ ደንበኞች አሁን በኤም-ፔሳ ኢንተርናሽናል ሪሚታንስ በኩል ወደ M-Pesa ኢትዮጵያ የሞባይል ገንዘብ ማስተላለፍ ይችላሉ ተብሏል።
በዚህ ትብብር፣ ሁለቱም ሀገራት ያሉ ደንበኞች የ M-Pesa ዋሌት ብቻ የሚያስፈልጋቸው ሲሆን ይህም በኬንያ የሚኖሩ እና የሚሰሩ ኢትዮጵያውያንን እንዲሁም በኢትዮጵያ የሚኖሩና የሚሰሩ ኬንያውያን ይጠቅማል ተብሏል።
የM-Pesa ኬንያ ደንበኞች ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ190 በላይ አገሮች በኤም-ፔሳ ግሎባል አገልግሎት አማካኝነት ገንዘብ መላክ እና መቀበል ይችላሉ ተብሏል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 5 ቀን 2017 ዓ.ም
