አለም አቀፍ የእጅ መታጠብ ቀን በአለም ለ 16ኛ በሀገራችን ለ11ኛ ጊዜ “ህይወቴን ለመጠበቅ እጄን በሳሙና እና በውሃ እታጠባለሁ”በሚል መሪ መልክት በሀገራችን እየተከበረ ነው።
የዩኒሊቨር ኢትዮጵያ ማኔጅንግ ዳይሬክተር ጆርጅ አውሱ እንሳ፤ የዘንድሮ የአለም እጅ የመታጠብ ቀን “ህይወቴን ለመጠበቅ እጄን በሳሙና እና በውሃ እታጠባለሁ” በሚል መሪ ቃል ይከበራል ብለዋል።
ዳይሬክተሩ፤ 80 በመቶ የሚሆኑት ጀርሞች ከሰው ወደ ሰው እንዲተላለፉና የበርካታ ኢንፌክሽን ምክንያቶችም የእጅ ንጽህና ጉድለት መሆኑን ተናግረዋል።
በባህሪ ለውጥ ላይ የሚያተኩረውና በላይፍቦይ ሳሙና አነሣሽነትና መሪነት የሚሰጠው የንጽሕና አጠባበቅ ትምሀርት፣ እስክ ጥቅምት ወር መጨረሻ ድረስ የሚቀጥል ሲሆን በመላው ኢትዮጵያ በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ጋር ለመድረስ ጥረት ይደረጋል ተብሏል ።
ልዑል ወልዴ
ጥቅምት 5 ቀን 2017 ዓ.ም
