ብጉንጅ/ boils

የበሽታ መከላከል አቅማቸው የተዳከመ ሰዎች በዚህ ህመም የመጠቃት እድላቸው ሰፊ መሆኑ ይገለጻል፡፡

በጉርምስና ዕድሜ ላይ በሚገኙ ወጣቶች እና ጎልማሶች ላይ ይህ ችግር በብዛት እንደሚስተዋል ባለሙያዎች ያነሳሉ፡፡

እንዲሁም ከሴቶች ይልቅ በወንዶች ላይ በብዛት እንደሚታይ ይጠቀሳል፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ ሙያዊ ማብራሪያ እንዲሰጡን ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊንየም ሜዲካል ኮሌጅ የቆዳና አባላዘር ክፍል – ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑትን ዶክተር ሳሚያ መተናን ናቸው ፡፡

ብጉንጅ ምንድን ነው ?

ብጉንጅ/ boils ማለት አንድና ከዚያ በላይ የሆኑ የፀጉር መዉጫ ቀዳዳዎች በባክቴሪያ ምክንያት ኢንፌክሽን በሚፈጥርበት ወቅት ቆዳ ስር በመቆጣት፣መግል በመያዝና በማበጥ ህመም እንዲከሰት የሚያደርግ ችግር ነዉ ይላሉ፡፡

እብጠቱ በፍጥነት በማደግና በመግል በመሞላት የህመም ስሜቱ እንዲጨምር ያደርጋል፡፡

መንስኤው ምንድን ነው ?

የበሽታው ዋነኛው መንስኤ” ስታፍሎኮካልስ” የተባለ የባክቴሪያ ዝርያ ሲሆን በአካባቢያችን በመገኘት ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋል

የስኳር ህመም እና የሰዉነት የበሽታ መከላከል አቅም መቀነስ ሌሎቹ ተጨማሪ መንስኤዎቹ መሆናቸውንም ይናገራሉ፡፡

ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?

  • ህመም ያለዉ እብጠት
  • በእብጠቱ ዙሪያ ያለው ቆዳ መቅላት
  • እብጠቱ መግል እየሞላዉ ሲመጣ የእብጠቱ መጠን መጨመር
  • ነጭ ወይም ቢጫ ነገር በእብጠቱ ጫፍ ላይ መታየት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ህክምናዎቹ ምንድን ናቸው

  • ቶሎ ቶሎ መታጠብ (ንፅህናን መጠበቅ )
    -የሚዋጡ እና በመርፊ የሚሰጡ ፀረ ባክቴሪያ መድሃኒቶችን መውሰድ
  • የመግል መቋጠር ሲያጋጥም ደግሞ በአነስተኛ ቀዶ ጥገና ማውጣት

በሽታው ወደ ሰውነት ውስጥ ሰርፆ ታችኛው የቆዳ ክፍል ላይ ከገባ ደግሞ ተኝቶ የመታከም ህክምና ሊሰጥ እንደሚችል አንስተዋል፡፡

በመጨረሻም ህብረተሰቡ ንፅህናውን በአግባቡ በመጠበቅ ከበሽታው እራሱን መከላከል እንዳለበት አና በሽታው ሲከሰት ቁስሉ ላይ በአድ ነገር ከመጠቀም መቆጠብ እንደሚያስፈልግ ዶ/ር ሳሚያ ተናግረዋል፡፡

አቤል እስጢፋኖስ

ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *