ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በብሪክስ (BRICS) የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ሩሲያ መግባታቸውን የአዘጋጇ የሩሲያዋ ታታርስታን ግዛት ፐሬዝዳንት ጽ/ቤት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
“የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ በ BRICS የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ካዛን ገብተዋል፤ በካዛን አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የግዛቷ ፕሬዝዳንት ሩስታም ሚኒካኖቭ አቀባበል አድርገውላቸዋል” ሲል መግለጫው አትቷል።
በካዛን በሚካሄደው የመሪዎች ስብሰባ ከ30 ሀገራት በላይ ተወካዮች ይታደማሉ መባሉን ከሩሲያ የዜና አገልግሎት ታስ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፤ የዩናይትድ አረብ ኤሚሬቱ ፕሬዝዳንት ቢን ዛይድ፣ የኢራኑ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽክያን፣ የህንዱ ፕሬዝዳንት ናሬንድራ ሞዲ በካዛን ከተገኙ መሪዎች ይገኙበታል።
ኢትዮጵያ በተያዘው የፈረንጆቹ 2024 መጀመሪያ ላይ ቡድኑን በይፋ መቀላቀሏ ይታወቃል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም
