የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ፣ “ተቀራርቦ መነጋገርን የመሰለ ነገር የለም” በማለት ከሕወሓት ሊቀመንበር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል በጋራ ከተነሱት ፎቶ ጋር በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።
ጌታቸው፣ ከሩቅ የሚመጣ ሰው አያስፈልግም በማለት ኹለቱን የሕወሓት ቡድኖች ለማገናኘት ጥረት በማድረግ ላይ የሚገኙ አካላትን አመስግነዋል።
ጌታቸው ከደብረጺዮን ጋር በምን ጉዳዮች ላይ እንደተነጋገሩ፣ መቼና የት እንደተገናኙ ወይም የትኞቹ አካላት እንዳቀራረቧቸው ግን አልገለጡም።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም
