ለአገራት የብድር መክፈል አቅም ደረጃ የሚያወጣው ዓለማቀፉ ፊች ሬቲንግስ፣ የኢትዮጵያን ብድር የመክፈል አቅም ከቀድሞው ደረጃ “ሲሲሲ ማይነስ” ወደ “ሲሲሲ ፕላስ” አሻሽሎታል።

ተቋሙ የኢትዮጵያን ብድር የመክፈል አቅም ደረጃ ያሻሻለው፣ በአገሪቱ ላይ የነበረው የገንዘብ ጫና በመቃለሉ፣ የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋት በመፈጠሩና በሂደት ላይ ያሉ የእዳ ሽግሽግ ድርድሮች ከኢትዮጵያ ብር ጋር ያልተያያዙ በመኾናቸው እንደኾነ ገልጧል።

በተያዘው በጀት ዓመት የመንግሥት የአገር ውስጥ ብድር ከአጠቃላይ አገራዊ ምርት አንጻር ወደ 0 ነጥብ 5 በመቶ ይወርዳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተቋሙ ገልጧል።

ባለፈው በጀት ዓመት የመንግሥት የአገር ውስጥ ብድር ከአጠቃላይ አገራዊ ምርት አንጻር 1 ነጥብ 7 በመቶ ደርሶ ነበር።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *