ከተመረጡ ትምህርት ቤቶች ለተወጣጡት አጠቃላይ ስልሳ ህፃናት እና አሰልጣኞችን በህፃናት አትሌቲክስ (Kids’ Athletics ) ንድፈ ሀሳብ ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል።
በኢ.አ.ፌ. ስልጠና ጥናትና ምርምር ዳይሬክተር ኢንስትራክተር ሳሙኤል ብርሃኑ እና ኢ.አ.ፌ ስልጠና ጥናትና ምርምር ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ጊዜ አድነው በጋራ በመሆን በህፃናት አትሌቲክስ ዙሪያ በመቀለ ዩኒቨርሲቲ ስር በሚገኘው ማህበረሰብ አቀፍ ትምህርት ቤት የተግባር ስልጠና በመስጠት አጠናቀዋል ።
የትግራይ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽ /ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ማሙ ለተሰጠው ስልጠና የላቀ ምስጋና በማቅረብ ድጋፍ እና ክትትል እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል ።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስልጠና ጥናት እና ምርምር ዳይሬክተር ኢንስትራክተር ሳሙኤል ብርሃኑ የክልሉ ፌዴሬሽን ላደረገው ሁለንተናዊ ድጋፍ እና ተሳትፎ የሚደነቅ መሆኑን በመጥቀስ ቀጣይም ተግባሩ ጠናክሮ እንደሚቀጥል አስገንዝበዋል ።
ጋዲሳ መገርሳ
ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም
