የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሩብ አመቱ 11.15 ቢሊየን ብር ገቢ ማስገባቱን ገለፀ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2017 የመጀመሪያ ሩብ አመት አፈፃፀሙ ከሀይል ሽያጭ እንዲሁም ከአዳዲስ ደንበኞች ወደ 11.55  ቢሊየን ብር ለማስገባት አቅዶ
11.15 ቢሊየን ብር ገቢ ማስገባቱን ገልጿል።

የተቋሙ ህዝብ ግግንኙነት ሀላፊ አቶ መላኩ ታዬ እንደገለፁት  ተቋሙ የሩብ አመት የአፈፃፀሙን እቅድ ወደ 97በመቶ አሳክቷል ብለዋል።

ገቢው የተገኘው ከሀይል ሽያጭ ከቋሚ ንብረቶች እንዲሁም ከአዳዲስ ደንበኞች የተገኘ ገቢ እንደሆነም ተገልጿል።

አቶ መላኩ ታዬ  የተገኘው ገቢ አዲሱን የታሪፍ ማሻሻያ ታሳቢ ያላደረገ እንደሆነም ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ተቋሙ  ወደ 120 ሺ ደንበኞችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ  አቅዶ  ወደ 90 ሺ ሰዎች አገልግሎቱን እንዲያገኙ አድርገናል ብሏል።

በዚህም የእቅዱን 75በመቶ ማሳካቱን አንስቷል።

በአዲሱ ሩብ አመት የዲሲፒሊን ግድፈትከ20 በላይ የተቋሙ ሰራተኞች ላይ እርምጃ መውሰዱንም ገልጿል።

በሩብ አመቱ የሀይል መቆራረጥ እና የደንበች ቅሬታ አሁንም አለመቀረፉን ሀላፊው አንስተዋል።

ተቋሙ አሁን ላይ አጠቃላይ ደንበኛችንም ወደ 4ሚሊዮን ገደማ ማድረሱ ተሰምቷል።

ለአለም አሰፋ

ጥቅምት 26  ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *