የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የመከላከያ ሚኒስትሩን ዮአቭ ጋላንትን አሰናበቱ
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የመከላከያ ሚኒስትራቸውን ዮአቭ ጋላንትን በአስደናቂ ሁኔታ ከስልጣናቸው ማባረራቸው ተሰምቱዋል ።
እርምጃው የተላለፈው ከሃማስ ጋር የተቀሰቀሰው የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት 14 ወራት ካለፈ በኋላ ነው።
በእርሳቸው እና በሚስተር ጋላንት መካከል “የመተማመን ቀውስ” ተፈጥሯል ብለዋል ሚስተር ኔታንያሁ።
ሁለቱ በጋዛ ጦርነት አካሄድ ላይ ብዙ ጊዜ ሲጋጩ ነበረም ተብሏል።
ልኡል ወልዴ
ጥቅምት 27 ቀን 2017
