ነዋሪ ያልገባባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውላቸውን ለማቋረጥ የወጣው ማስጠንቀቂያ እስከ ህዳር 30  2017 ዓ.ም ድረስ ተራዘመ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን  በተለያዩ ጊዜያት በሽያጭ ተላልፈው የቤት ባለቤቶች  ውል የተዋዋሉባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች እስከ አሁን ነዋሪ ባለመግባቱ ምክንያት የተለያዩ ህገ ወጥ ተግባራት እየተፈፀመባቸው እና ለፀጥታ ስጋት እየሆኑ ይገኛል ማለቱ ይታወሳል።

በመሆኑም  ነዋሪ ያልገባባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች እስከ ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም ድረስ  ባለቤቶቹ ወደ ቤታቸው እንዲገቡ ኮርፖሬሽኑ እያስጠነቀቀ የነበረ ሲሆን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ህዳር30 2017አ ም እንደተራዘመ አስታውቋል።

ሆኖም  በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ የማይገቡ ነዋሪዎች የሽያጭ ውላቸው የሚቋረጥ  መሆኑን እና በእጣ እና በሽያጭ ለሌላ ነዋሪ የሚተላለፉ መሆኑን ኮርፖሬሽኑ ገልጿል

ለዓለም አሰፋ

ጥቅምት  30 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *