የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት፤ የኮምንኬሽን ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሰናይት ሰለሞን ፤የዘንድሮ የብሄር ብሄረሰቦች ህዝቦች ቀን’’የሃገራዊ መግባባት ለህብረ ብሄራዊ አንድነት ’’ በሚል መሪ ቃል ይከበራል ብለዉናል፡፡
የዘንድሮ የብሔር ብህሄረሰቦች ህዝቦች ቀን ለ19ኛ ጊዜ በአርባምጭ ከተማ እንደሚከበር ነግረዉናል።
ወ/ሮ ሰናይት በዓሉን ለማክበር ወደ አርባምንጭ የሚመጡ እንግዶችን ተቀብሎ ለማስተናገድ ከአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር እንዲሁም ከአከባቢዉ ማህበረሰብ ጋር ዉይይቶች መደረጋቸዉን ለጣቢያችን ተናግረዋል።
ሀላፊዋ አገልግሎት ይሰጣሉ ተብለዉ በተለዩ ሆቴሎች፤በበዓሉን ለመታደም በሚመጡት እንግዶች ላይ ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ እንዳያደርጉ፤በአገልግሎት ጥራትና ይዘት እንዲሁም በሚሰጡት መስተንግዶ ዙሪያ ጥብቅ ቁጥጥር የሚያደርጉና እርምጃ የሚወስዱ ኮሚቴ ተዋቅሯል ብለዋል፡፡
የበዓሉ አላማ በየዓመቱ ህዳር 29 ቀን አሁን በሥራ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ሪፖብሊክ ህገ መንግሥት የጸደቀበት ቀንን ምክንያት በማድረግ ሁሉም በባህሉ አምሮ ደምቆ በእኩልነት የሚያከብረዉ ነዉ ፡፡
በመጨረሻም በበዓሉ አገር አቀፍ ሲምፖዚየሞች፣ ኤግዚቢሽኖች፣ ስልጠናዋች እና የባህል ልውውጦች እንደሚካተቱ ተገልጿል ።
ልዑል ወልዴ
ህዳር 3 ቀን 2017 ዓ.ም
