አልሸባብን የማዳከም ስራ እንደሚቀጥል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ

በሶማሊያ የሚገኘውን አሸባሪ ቡድን አልሸባብ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ሥጋት እንዳይሆን “በየትኛውም ሁኔታ አሸባሪ ቡድኑን የማዳከም ሥራ የሚቀጥል ይሆናል” ሲል መንግሥስት አስታወቋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ዛሬ በሰጡት መግለጫ ሶማሊያ የኢትዮጵያ ሠራዊት በአዲሱ የአፍሪካ ሕብረት የድጋፍ እና የማረጋጋት ተልዕኮ ውጪ መሆኑን ባለፈው ሳምንት በይፋ ማስታወቋን በተመለከተ የኢትዮጵያን አቋም ሲጠየቁ ነው ይህንን ያሉት።

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ “የማይነጣጠሉ ሕዝቦች እንደመሆናቸው ጊዜያዊ ችግሮችን የመባባስ ፍላጎት የለንም” ያሉት ቃል አቀባዩ የሶማሊያ ማንግሥት ይፋ ላራመደው አቋም አልሸባብን እናዳክማለን ከማለት በቀር ቀጥተኛ ምላሽ አልሰጡም።

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የተካረረ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ውስጥ እንዲገቡ ምክንያት የሆነው የኢትዮጵያ እና የራስ ገዟ ሶማሊላንድ «የባሕር በር እውቅና» የመግባቢያ ስምምነት እስካሁን በሂደት ላይ መሆኑ ሲገለጽ በአንድ በኩል፣ አልሸባብን በመዋጋት ለዓመታት የጋራ ግብ እና ጥብቅ ወዳጅነት የነበራቸው ኢትዮጵያ እና ሶማሊያን ሆድና ጀርባ አድርጎ ከቃላት ያለፈ የዲፕሎማሲ ውጥረት ውስጥ ከቷቸዋል።

ህዳር 05 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *