የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ሲጠበቅ የነበረውን የ 2017 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት ተጨማሪ 582 ቢሊዮን ብር በጀት አፅድቋል።
ከዚህ በጀት ዉስጥ 282 ቢሊዮን ያህሉ ከግብር እንደሚሰበሰብ የገለፀ ሲሆን ይህም የንግድ ዘርፉን በይበልጥ አለመረጋጋት ዉስጥ እንደሚከተዉ እና የኑሮ ዉድነቱን ሊያባብሰዉ እንደሚችል ከምክርቤት አባላት ጥያቄ አስነስቷል ።
የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላት እንደተናገሩት ” ይህ ከፍተኛ ታክስ በነጋዴው ላይ ጫና እፈጠረ ከመሆኑ በላይ የንግዱ ማህበረሰብን መደናገር” ዉስጥ በይበልጥ እየከተተው መሆኑን አስረድተዋል ።
ገቢን ለመጨመር በሚል የታክስ ጫናዉን ከልክ በላይ መለጠጥ በንግድ እንቅስቃሴ ላይ ችግር ሊያመጣ እንደሚችል እነዚሁ የምክርቤት አባላት ተናግረዋል።
የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴም በበኩላቸው በሰጡት ምላሽ የተደረገው ” ከማሻያው በፊት ባለው መቀጠል የሀገርን ኦኮኖሚ እያደሙ መቀጠል እና ወደ ለየለት የኢኮኖሚ ውድቀት የሚያመራ በመሆኑ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያም ጊዜውን የጠበቀ መሆኑን አስረድተዋል ሲል ካፒታል ዘግቧል ።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ኀዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም
