የመንጋጋ አጥንት መገጣጠሚያ ቴምፖራል ከተባለ የራስ ቅል አጥንት ጋር የሚያገናኝ ማጠፊያ ነው።
ይህም ማውራት ፣ ማኘክ እና ማዛጋት እንዲችሉ ፤ መንጋጋን ወደ ላይና ወደ ታች እንዲሁም ከጎን ወደ ጎን እንዲያንቀሳቅሱ ያስችላል።
ይሁን እና በዚህ በመንጋጋ መገጣጠሚያ ላይ በሚደርስ ችግር በአለማችን ላይ ቁጥራቸዉ ቀላል የማይባሉ ሰዎች እንደሚሰቃዩ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
ይህ ህመም በጊዜ መታከም ካልተቻለ ከፍተኛ ችግር የሚያስከትል የህመም አይነት ነዉም ተብሏል፡፡
በመንጋጋ መገጣጠሚያ ላይ ህመም እና መታወክን ሲኖር የእለት ተእለት ስራን የሚያውክ ከባድ ችግር እንደሆነም ነዉ የተነገረዉ ፡፡
ለመሆኑ የመንጋጋ ህመም ለመከሰቱ ምክኒያት ምንድነዉ ህክምናዉስ ስንል በአዲሲ አበባ ዩኒቨረሲቲይ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ፤የመንጋጋ፤ የአፍ ዉስጥና የፊት ቀዶ ህክም፤ እንዲሁም የጥርስ ህክምና ትምህርት ክፍል ሃላፊ ዶክተር ዳንኤል ሹካሬን ጠይቀነል፡፡
የመንጋጋ መገጣጠሚያ ህመም በአብዛኛው ሴቶች ላይ እንዲሁም ወጣትና አረጋውያን ላይ ይከሰታል።
የመንጋጋ መገጣጠሚያ ህመም ለመከሰቱ ምክንያቶቹ ;-
-በአብዛኛው በፊት ላይ በሚፈጸም ድብደባ
-አገጭ ላይ ምት ሲኖር ወይም ሌላ ጉዳት ሲኖር የሚሉት ይተቀሳሉ፡፡
-ኢንፌክሺኖች
-ጠንካራ ነገር ማኘክ ወይንም መጋጥ
-የተፈጥሮ የጥርስ አበቃቀል
-አብዝቶ ማሲቲካ ማኘክ አጋላጭ ምክንያት ናቸዉ የተባለሲሆን ፤
ከዚኅ ባለፈ እንደዚህ ዓይነት ህመሞች÷ የመገጣጠሚያ ጉዳት፣ በጡንቻ መቆጣት እንዲሁም በአጥንት ላይ የሚደርስን ጉዳት ተከትሎ ይከሰታሉ፡፡
እንዲሁም የጥርስ ሙሌት ከፍ ተደርጎ ሲሞላ፣ በትክክል ያልተሰራ ሰው ሠራሽ ጥርስ፣ የጥርስ መፋጨት፣ ጭንቀትና ድባቴ ለመንጋጋ መገጣጠሚያ በምክንያትነት ይጠቀሳሉ፡፡
የመንጋጋ መገጣጠሚያ ህመም ምልክቶች፤-/
የዚህ ህመም ምልክት መገጣጠሚያ ላይ እንዲሁም ከመገጣጠሚያው ውጭ ሊታዩ ይችላል እንደ ባለሙያዉ ማብራርያ።
ከምልክቶቹ መካከል፤- አፍን እንደወትሮ ለመክፈት መቸገር፣ የመገጣጠሚያ ህመም መሰማት፣ ምግብ ሲታኘክ ድምፅ መሰማት፣ አፍ ተከፍቶ አልዘጋም ማለት፣ የመገጣጠሚያ አካባቢ እብጠት፣ የጆሮ መጮህ እና ራስ ምታት ይጠቀሳሉ፡፡
በተጨማሪም የአገጭ መገጣጠሚያ ህመም፣ የአንገት እንዲሁም የጭንቅላት ጡንቻ ህመም፣ እንቅልፍ የመተኛት ችግር፣ ጥርስን ማፋጨት የመንጋጋ ህመም ምልክቶች ናቸው፡፡
ለመንጋጋ ህመም የሚደረጉ ህክምና ፤-
ሕክምናው እንደ ህመሙ ደረጃ የሚወሰን ሲሆን፤
እንደ ህመሙ ሁኔታ እና ግለሰዎቹ ወደህክምና ተቋም እንደሄዱበት ፍጥነት የህክምና እርዳታ ይደረጋል ተብሏል፡፡
ቀላል እና በጊዜ ወደ ህክምና ተቋም ከተኬደ ፤-የህመም ማስታገሻ፣ ጥርስ ላይ የሚደረግ መሸፈኛ፣ የመገጣጠሚያ እጥበት፤ፊዚዮ ቴራፒ ፤የመዳኒት ህክምና ይሰጣል፡፡
ከረፈደ ወደህክምና ለሚሄድ እና የህመሙ ሁኔታ ታይቶ የቀዶ ጥገና ሕክምና ይሰጣል፡፡
በመጨረሻም:-
የመንጋጋ፤ የአፍ ዉስጥና የፊት ቀዶ ህክም፤ እንዲሁም የጥርስ ህክምና ትምህርት ክፍል ሃላፊዉ ዶክተር ዳንኤል ሹካሬ፤ማንኛውም የመንጋጋ ህመም ያጋጠመዉ ሰዎ በፍጥነት ወደ የአፍና የከፍተኛ ህክምና ባለሙያ መቅረብ እንዳለበት ተነግሯል።
ለመንጋጋ ህመም ያለው አመለካከት ሕመሙን በሚያስከትሉ መሠረታዊ ምክንያቶች ላይ የተመሠረተ ነው።
ህመሙ ችላ ቢባል ፤ምግብ መብላት አለመቻልን ጨምሮ ንግግርን በማቋረጥ ከማህበራዊ ግንኙነት ይገድባል ተብሏል፡፡
በተጨማሪም የመንጋጋ በሽታ የሚያመጣው ህመም ተባብሶ ለማከም የበለጠ አስቸጋሪ የሆነ ደረጃ ላይ ሊደርስ እንደሚችልም ጠቁሟል፡፡
ልኡል ወልዴ
ኀዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም
