አቶ ጌታቸው ረዳን እንደሚከስ አስታውቆ የነበረው የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም  መቀሌ ቅርንጫፍ ሃሳብ ቀይሪያለሁ አለ

የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም  መቀሌ ቅርንጫፍ  “በቀድሞ የትግራይ ፖሊስ አባላት” ጉዳይ ከፕሬዝዳንቱ ጋር  ተገናኝተው ለመምከር ቀጠሮ መያዛቸው ተነግሯል ።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም መቀሌ ቅርንጫፍ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ   ላይ ሊመሰርት የነበረውን ክስ በመተው ክፕሬዝዳንቱ ጋር ለመነጋገር  ቀጠሮ መያዙን ገልጿል።

የትግራይ ቅርጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፀሀዬ እምባዬ  ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት  ጉዳዩ በካቢኔ እንደተወሰነ ነግረውን ፤ ጊዜያዊ አስተዳደሩ የቀድሞ ፖሊሶችን አቤቱታ በተመለከተ በካቢኔው በኩል ተወስኖ  ከፕሬዝዳንቱ ጋር ለንግግር ሊቀመጡ እንደሆነ ነግረውናል።

አሁን ላይ በአማካሪ በኩል  ጉዳዩ ለካቢኔ ተመርቶ ውሳኔ የተሰጠ ሲሆን በአማካሪያቸው በኩል  በሶስት ቀናት ውስጥ ንግግሩን ለማድረግ መታቀዱን አስታውቀዋል ።

በጊዜያዊ አስተዳደሩ ላይ የቀረበው ክስ፤ የቀድሞ የትግራይ ፖሊስ አባላት አለአግባብ ከሥራ ገበታቸው የተባረሩ በመሆኑ ወደ ነበሩበት ቦታ እንዲመለሱና ደሞዛቸውም እንዲከፈላቸው” የሚል ነው፡፡

ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኃላ ሁሉም የመንግሥት ሠራተኛ ወደ ሥራ የተመለሰ መሆኑን ያነሱት አቶ ፀሐዬ፤ ፖሊሶቹ ግን ደምወዝ እንዳላገኙና ወደ ሌላ ሥራም እንዳይገቡ  መሸኛ ጭምር እንዳልተሰጣቸው  ነግረውናል፡፡

ለአለም አሰፋ

ኀዳር 25 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *