የሶርያ መንግስት ወታደሮች የተወሰነ ግዛትን ማስመለሳቸውን ቢገልፁም ፤ አማፅያኑ አራት ማዕከላዊ ከተሞችን ይዘዋል ተብሏል ።
የሶሪያ አማፅያን ድል እየተቀዳጁ መሆኑም ነው የተዘገበዉ።
የተቃዋሚ ተሟጋቾች እንዳሉት ወደ ሃማ ከተማ ለመግባት የሚያግዙ አራት ቦታዎችን አማፂያኑ የተቆጣጠሩ ሲሆን፤ ይህም ወደ ማእከላዊ ሃማ ለመግባት የሚያስችላቸዉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የአማፅያኑ ቡድኖች ዋና ደጋፊ የሆኑት የቱርኩ ፕሬዝዳንት ኤርዶሃን ፤ የሶሪያ መንግስት ሁኔታው የበለጠ እንዳይባባስ ለመከላከል ከፈለገ “በእውነተኛ የፖለቲካ ሂደት ውስጥ” መሳተፍ አለበት ካሉ በኋላ አመጹ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገልጿል፡፡
የሶርያ የእርስ በርስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ የበሽር አል አሳድ መንግሥት በአማጽያኑ ከተነጠቀው የሀገሪቱ ግዛት ሁለት ሦስተኛውን መልሶ ከእጁ ማስገባት ችሎ ነበር ተብሏል ዘገባዉ የኤፒ ነዉ ።
ልዑል ወልዴ
ኀዳር 25 ቀን 2017 ዓ.ም
