ዘምዘም ባንክ ከሳንቲም ፔይ ፋይናሺያል ሶልዩሽን ጋር የQR ኮድ ፔይመንት መጀመራቸውን አስታወቁ

ዘምዘም ባንክ   እና ሳንቲምፔይ ፋይናሻል  ሶሊዩሽን  የአጋርነት ፊሪማ በዛሬው እለት ተፈራርመዋል፡፡

የዘምዘም ባንክ  ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ መሊካ በድሪ  ባንኩ የተቋቋመው በሃይማኖታዊ እምነት ወይም በሌሎች ምክንያቶች ከፋይናስ  ስርዓቱ  የራቀውን የህብረተሰብ ክፍል ልዩ ትኩረት በማድረግ የፋይናስ  አካታችነትን ለማሳደግ ነው ብለዋል፡፡

ባንኩ በቀጣይ የወደፊቱን የዲጂታላይዜሽን ዘመን ከግምት በማስገባት እንዲሁም ጊዜንና ወቅቱን ያማከለ የፋይናስ  ስርዓቶችን  ለህዝብ ተደራሽ ለማድረግ ሰፊ ዕቅድ ይዞ እየሰራ ይገኛል ብለዋል ዋና ስራ አስፈፃሚዋ፡፡

ወ/ሮ መሊካ ፤ዛሬ ከሳንቲምፔይ ፋይናንሺያል ሶልዩሽን አክሲዮን ማኅበር ጋር ያደረግነው የአጋርነት ስምምነት  የክፍያ ሥርዓቱን ለማሳለጥ ይረዳናል ብለውናል።

የሳንቲምፔይ ፋይናንሻል ሶሉሽን አ.ማ. ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ትንሳኤ ደሳለኝ በበኩላቸው ፤ሳንቲምፔይ ክፍያዎችን ለመፈጸምና ሌሎች አስፈላጊ የፋይናንስ አገልግሎቶችን ለተጠቃሚዎች ለማቅረብ የሚያስችል መጠነ ሰፊ አገልግሎት የሚሰጥ ዘመናዊ የክፍያ መፈጸሚያ መንገድ ነው ብለዋል።

አቶ ትንሳኤ አሁን ላይ በክፍያ መፈጸሚያ ስረአቱ በአንድጊዜ የገንዘብ ዝውውር የሚያደርጉ ከ8 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን ሳንቲምፔይ እያስተናገደ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ኩባንያው እስካሁን ቴሌ ብር፣ ሲቢኢ ብርን ጨምሮ ወደ አሥር ከሚሆኑ ባንኮች ጋር አብሮ እየሠራ መሆኑ አስታውቀዋል፡፡

በእዚህና በሌሎች የክፍያ አማራጮች ገንዘብ መክፈል የሚቻልበት ዕድል ስለተፈጠረ ሁሉንም ባንኮች በአንድ ላይ አያይዞ ለደንበኞች አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም ዘምዘም ባንክ  ዘመኑን የዋጀ ዲጂታል የክፍያ አማራጮችን ሺቶ ከእኛ ጋር በመስራቱ ደስብሎናል ሲሉ ተናግረዋል ።

ልኡል ወልዴ

ኀዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *