ከፆታዊ ጥቃት ጋር በተያያዙ ወደ ፍርድ ቤት የሚመጡ አቤቱታዎች በአመት 10ሺ አይሞሉም ተባለ

ይህ የተገለፀው በአለም አቀፍ ደረጃ ለ33ኛ ጊዜ በኢትዮጲያ ደግሞ ለ19ኛ ጊዜ አለም አቀፍ የፀረ ፆታዊ ጥቃት ቀን “የሴትዋ ጥቃት የኔም ነው ዝም አልልም” በሚል መሪ ቃል በተካሄደ የፓናል ውይይት ላይ ነው።

በፍትህ ሚኒስትር የሴቶች እና ህፃናት ጉዳዮች ዳይሬክተር ወ/ሮ ዳግማዊት ተረፈ ፤ በኢትዮጵያ ከፆታዊ ጥቃት ጋር በተያያዙ ወደ ፍርድ ቤት የሚመጡ አቤቱታዎች (ኬዞች ) በአመት 10ሺ አይሞሉም ብለዋል።

ይህ ማለት ግን ፆታዊ ጥቃቱ ቀንሶ ሳይሆን ጉዳዩን ወደ ህግ ለማምጣት የሚደረገው ጥረት በተለያዩ ምክንያቶች አናሳ በመሆኑ ነው ሲሉ ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።

እንደ ምክንያት የሚነሳው ደግሞ አቤቱታዎች ጥቃቱ የደረሰባቸውን ሰዎችን ተከታትሎ ጉዳያቸውን ወደ ህግ ለማምጣት ሚያደርግ ተቋም አናሳ በመሆኑ እንደሆነም ተነስቷል።

ከፆታዊ ጥቃት ጋር በተያያዘ የህግ ስርአቱ ቢኖርም ትግበራው የጎላ አደለም የተባለ ሲሆን ይህንን ማስተካከል እንደሚገባ ተተግሯል።

ህጉ ክፍተት እንዳለው ቢሆንም የህጉ ትግበራው ግን መሻሻል አለበት ሲሉ በፍትህ ሚኒስትር የሴቶች እና ህፃናት ጉዳዮች ዳይሬክተር ወ/ሮ ዳግማዊት ተረፈ ተናግረዋል።

ብዙ ጊዜ አቤቱታ ለማቅረብ የሚደፍሩ ተጠቂዎች አናሳ ናቸው የሚሉት ወ/ሮ ምዕራፍ እሱን ከሚመለከተው አካላት ጋር በመሆን ማስተካከል እንዳለበት አንስተዋል።

በአለም ከሶስት ሴቶች በአንዷ ላይ የፆታዊ ጥቃት እንደሚደርስም የአለም አቀፍ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ለዓለም አሰፋ

ኀዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *