በሽር አላሳድን ከስልጣን ያስወገደችዉ አገረ ሶሪያ ሞሃመድ አልበሽርን ጊዚያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጋ ሾማለች፡፡
አልበሽር የሽግግር መንግስት እንዲመሰርቱ ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል ነዉ የተባለዉ፡፡
በበሽር አላሳድ የስልጣን ዘመን ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነዉ ያገለገሉት ሙሃመድ አል ጃላሊ የሽግግር መንግስቱን እንደሚደግፉ ቃል ገብተዋል፡፡
ጊዚያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር ሖነዉ የተመረጡት ሞሃመድ አልበሽርም አገሪቱን ለማረጋጋት በሚደረገዉ ጥረት ሁሉም አጋርነቱን እንዲያሳይ ጠይቀዋል፡፡
አባቱ መረቀ
ታኅሣሥ 2 ቀን 2017 ዓ.ም
