በኢትዮጵያ ያለ ህግ አግባብ የታሰሩ ኤርትራውያን እንደሌሉ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አስታወቀ።

መስሪያ ቤቱ በርካታ ኤርትራውያን በህገወጥ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ ገብተው ከተፈቀደላቸው ጊዜ በላይ በመቆየት ለውጭ አገር ዜጎች ባልተፈቀዱ የስራ መስኮችን ጨምሮ በኮንትሮባንድ፣ በህገወጥ ሰው ዝውውር እና በሌሎች ህገወጥ ተግባሮች ተሰማርተው የሚገኙ እንዳሉ ጠቅሶ እነዚህ በህግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ ገልጿል።

በኢትዮጵያ በተለይም በአዲስ አበባ በኤርትራውያን ላይ የጅምላ እስራት እየተካሄደ እንደሆነ ቢቢሲ ትግርኛ ያነጋገራቸው በርካታ በከተማዋ የሚኖሩ ኤርትራውያን ከዚህ ቀደም መግለጻቸው ይታወሳል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ባወጣው መግለጫ ኤርትራውያን ስደተኞች ላይ ያነጣጠረ ከሃገር ማባረርም ሆነ እስር እንዳልተፈጸመ ገልጾ ነገር ግን “የሃገርን ብሔራዊ ደህንነትና ጥቅም በሚጎዳ መልኩ ህገወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው የሚገኙ የውጭ አገር ዜጎች” ላይ ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደ እንደሆነ አሳስቧል።

በህገወጥ መንገድ ወደ አገር የገቡ ኤርትራውያንን መስሪያ ቤቱ ወደ ህጋዊ መንገድ ለማስገባት በተደጋጋሚ ጥሪ ቢያደርግም የተመዘገቡት ውስን ናቸው ብሏል።

ሆኖም ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድና የስራ ፈቃድ ሳይኖራቸው፣ በሃሰተኛ ማንነት ለውጭ አገር ዜጎች ባልተፈቀዱ የስራ መስኮች ከትንሽ ሱቅ ችርቻሮ እስከ ትላልቅ ስራዎች በህገወጥ መንገድ ተሰማርተው እንደሚገኙ አጽንኦት ሰጥቷል።

ታህሣሥ 4 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *