የቼልሲው ኮኮብ ሙድሪክ በአበረታች ንጥረ ነገር ምከንያት ከእግርኳስ ታገደ !

ዩክሬናዊው የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የፊት መስመር ተጨዋች ማይካሎ ሙድሪክ ያልተፈቀደ አበረታች ንጥረ በውስጡ መገኘቱ ተገልጿል።

የእንግሊዝ እግርኳስ ማህበር ባደረገው ምርመራ ” positive ” ሆኖ መገኘቱ የተገለጸው ተጨዋቹ በጊዜያዊነት ከእግርኳስ መታገዱን ክለቡ አሳውቋል።

ማይካሎ ሙድሪክ እያወቀ የተከለከለ ንጥረ ነገር አለመውሰዱን ማረጋገጡን ቼልሲ ባወጣው መግለጫ አስታውቀዋል።

ተጨዋቹ ያለፉት አምስት የክለቡ ጨዋታዎች እንዳመለጡት የሚታወስ ሲሆን አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ በህመም እንደሆነ ገልፀው ነበር።

ቼልሲዎች በመግለጫቸው በተጫዋቾቻችን ላይ ሁልጊዜም በሚደረገው መደበኛ ምርመራ ማይካሎ ሙድሪክ ያልተለመደ ንጥረነገር መጠቀሙን ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል።

ይሆን እንጂ ተጨዋቹ እንዳለው ኤፍኤው ከእኔ በወሰደው ናሙና የተከለከለ ንጥረ ነገር ተጠቅመሀል ሲል መልዕክት ደርሶኛል ነገርግን እኔ ምንም አይነት ተጨማሪ ነገር ተጠቅሜ አላውቅም።

እኔ ምንም አይነት የእግርኳስ ህግጋትን ስላልጣስኩ ይህ አስደንጋጭ ሆኖብኛል ፤ በቅርቡ ወደ ሜዳ እንደምመለስ ተስፋ አደርጋለሁ ብሏል።

ጋዲሳ መገርሳ

ታኀሣሥ 8 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *