በግጭት ውስጥ ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው ያሉ ሴቶች ችግራችን በሀገራዊ ምክክሩ መፍትሔ  ያገኛል ብለን እንጠብቃለን ሲሉ የኦሮሚያ ክልል የሴት ተወካዮች ተናገሩ  ።

በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ባለው የምክክር መድረክ ላይ ኢትዮ ኤፍ ኤም ያነጋገራቸው የሴት ተወካዮች ምክክሩ በሴቶች ላይ የሚፈፀመው በደል ይፈታል ብለን እንጠብቃለን ብለዋል ።

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አከባቢዎች ባሉ ግጭቶች ቀዳሚ ተጠቂዎች ሴቶች መሆናቸውን የነገሩን የሴት ተወካዮቹ ፤ግጭቶች በምክክር ተፈተው በሴቶች ላይ ያሉ በደሎች ያበቃሉ ብለን እንጠብቃን ሲሉ ለጣቢያችን ተናግረዋል ።

ግጭት ባለባቸው የኦሮሚያ አከባቢዎች ሴቶች እየተጎዱ መሆኖቸውን ተሳታፊዎቹ አስረድተዋል።

አሁን የተጀመረው ሀገራዊ ምክክር ከዚህ በፊት ለተፈፀሙና እየተፈፀሙ ላሉ በደሎች መፍትሔ ይሰጣል ብለን እንጠብቃለን ብለዋል።

ከዚህ በፊት በሴቶች ላይ ይደርሱ የነበሩ የፖለቲካ፣የኢኮኖሚና የማህበራዊ መገለሎች እንዲያበቁ ሴቶችም በፖለቲካ እንዲሳተፉ ምክክሩ  ይረዳል ብለን እናስባለን ሲሉ ነግረውናል።

ልዑል ወልዴ

ታኀሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *