በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሚወሰኑ የፍቺ እና ጉዲፈቻ ውሳኔዎች በይፋ አገልግሎት መጀመራቸዉ ተገለጸ፡፡

በፍርድ ቤቶች የምዝገባው አገልግሎት በይፋ በአራዳ እና ቦሌ ምድብ ችሎቶች መጀመሩም ተሰምቷል፡፡

የሲቪል ምዝገባ  እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከሚመዘግባቸው ኩነቶች መካከል በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሳኔ የሚሰጥባቸው ጉዲፈቻ እና ፍቺ በፍርድ ቤቶቹ መመዝገብ መጀመራቸዉ ተገልጿል፡፡

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ፤ በአንድ ማዕከል አገልግሎቱ ከፍቺ እና የጉዲፈቻ ምዝገባ አገልግሎት በተጨማሪ የፋይዳ ምዝገባ በፍርድ ቤቶቹ እንደሚከናወን ጠቅሰዋል፡፡

በዕለቱ መርሃ ግብር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ-አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ፣ የፌደራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ፉዓድ ኪያር፣ የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ዮዳሄ ዘሚካኤል እንዲሁም የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ተገኝተዋል።

አፎሚያ አሸናፊ

ታኀሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *