ዕድሜያቸው ከ6 ወር በላይ ከሆኑ ልጆች 8 በመቶዎቹ ብቻ ከእናት ጡት ወተት ውጪ ተጨማሪ ምግቦችን እንደሚጀምሩ ሰምተናል።
61 በመቶ የሚሆኑ እናቶች ብቻ ልጆቻቸውን እስከ 6 ወር ድረስ ጡት እንደሚያጠቡም ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
የተለያዩ ማስታወቂያዎች እና የተጋነኑ መረጃዎች እናቶች ልጆቻቸውን ጡት እንዳያጠቡ አድርጓል ነው የተባለው ።
በአዲስ አበባ 57 በመቶ የሚሆኑ እናቶች በተለያዩ ማስታወቂያዎች ምክንያት ልጆቻቸውን ጡት አያጠቡም ተብሏል።
ከ6 ወር በላይ ለሆናቸው ልጆች የሚሰጥ ምግብ ላይ የስኳር እና የቅባት መጠን አነስተኛ መሆን ያለበት ቢሆንም በጥናት የታየው ግን የዚህ ተቃራኒ መሆኑም ተገልጿል።
በአገራችን ዕድሜያቸው 6 ወር እና ከዛ በላይ የሆኑ ህፃናት 31 በመቶ ለጤናቸው ተስማሚ ያልሆኑ ጣፋጭ መጠጦችን የሚጠቀሙ ሲሆን ፤ 15 በመቶዎቹ ጤናማ ያልሆኑ ምግቦችን ይመገባሉ።
74 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ምንም ዓይነት አትክልትና ፍራፍሬ እንደማይመገቡ ጤና ሚኒስቴር ገልጿል።
በሶማሌ ክልል ዕድሜያቸው ከ6 ወር በላይ የሆኑ 91 በመቶ ህፃናት ምንም ዓይነት አትክልት እና ፍራፍሬ አያገኙም።
በአጠቃላይ በከተማ 50 በመቶ የሚሆኑ ዕድሜያቸው ከ6 ወር በላይ የሆኑ ህፃናት ለጤናቸው ተስማሚ ያልሆኑ ጣፋጭ መጠጦችን የሚወስዱ ሲሆን፤ በገጠር ከሚገኙት ደግሞ 23 በመቶዎቹ ይህን እንደሚጠቀሙ ተገልጿል።
እስከዳር ግርማ
ታኀሣሥ 11 ቀን 2017 ዓ.ም
