ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በአሶሳ ከተማ የኔትዎርክ ዝርጋታ ማድረጉን አስታወቀ፡፡

የኔትዎርክ ዝርጋታዉ፤ ኩባንያዉ አስተማማኝ እንዲሁም ከፍተኛ ጥራት ያለዉን የግንኙነት መስመር በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል ለማዳረስ ያለዉን ቁርጠኝነት ያሳያል ብሏል፡፡

ባለፉት 2 ሳምንታት በምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በሚገኙ ነቀምቴ፣ ጋምቤላ፣ መቱ እና በደሌ ከተሞች የኔትዎርክ ዝርጋታ ማድረጉን አስታዉሷል፡፡

የዛሬዉ የኔትዎርክ ዝርጋታ ኩባንያዉ በክልሉ እየሰራ ያለዉን ስራ የሚያጠናክር መሆኑንም ገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ ስራ ከጀመረ ሁለት ዓመታትን ያስቆጠረዉ ሳፋሪኮም፤ በማዕከላዊ፣ ሰሜን፣ ደቡብ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ የአገሪቱ ስፍራዎች ከግማሽ በላይ የሚቆጠር ህዝብ ተደራሽ አድርጌያለሁ ብሏል፡፡

ኤዉሮፕላን ማረፊያዉን ጨምሮ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና አከባቢዉ ላይ ለሚገኙ ዜጎች የ4ጂ ኔትዎርክ ተደራሽ እያደረገ መሆኑንም ገልጿል፡፡

የሳፋሪኮም አገልግሎቶችን እንዲሁም የጥገና ስራዎችን የሚሰሩ ማከፋፈያ ሱቆችን በምዕራብ ኢትዮጵያ በሚገኙ ከተሞች መክፈቱን የገለጸዉ ኩባንያዉ፤ ወደ 6 መቶ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠሩንም አስታዉቋል፡፡

እስከዳር ግርማ

ታኀሣሥ 18 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *