የጥምቀተ ባህር የታቦታትት ማደሪያ ቦታዎች አከባቢ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ውይይት ተደረገ

የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ፤ የአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ እና የአዲስ አበባ ሀገር ስብከት ዘንድሮ የሚከበረውን ጥምቀተ ባህር የታቦታትት ማደሪያ ቦታዎች አከባቢ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ውይይት አድርጊያለሁ ብሏል፡፡

ቢሮው በማህራዊ ትስስር ገጹ ባሰራጨው መረጃ የጥምቀት በዓል በተባበሩት መንግስታት የሳይንስና የባህል ማዕከል በዓለም በማይዳሰሱ ቅርሶች የተመዘገበ የዓለም ቅርስ እንደመሆኑ መጠን በዓሉን ለማክበር ከተለያዩ የዓለም ጫፎች በርካታ ቱሪስቶች የሚሳተፉ በትና ዓለማቀፍ ሚዲያዎች የአየር ሽፋን ለመስጠት የሚታደሙበት ስለሆነ እንደ ሃገር የሚሰጡት ኢኮኖሚያዊና ዲፕሎማሲያዊ ጥቅሞች ከፍተኛ መሆኑ በውይይቱ ትኩረት ያገኘ እንደነበረ አመልክቷል፡፡

በዘንደሮ ዓመት የሚከበረው የጥምቀት በዓል ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ፤ የታቦታት ማደሪያ አከባቢ የሚታዩ የቦታ እጥረቶችና በዓሉ በሰላም እንዳይከበር የፀጥታ ስጋት ምልክቶችን ቀድሞ በመለየት ለችግሮች መፍትሄ ለማዘጋጀት የሚረዳ ውይይት ስለመሆኑም ተጠቅሷል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ የመልካም አስተዳደር ችግሮችና በዓሉን በሰላም ለማክበር እንደ እንቅፋትወይንም ፀጥታ ስጋት ሊወሰዱ የሚችሉ ጥቃቅን ጉዳዮች በአስቸኳይ እንዲፈቱ የበሮ ኃላፊዋ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲያልፍ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳበትም አሳስበዋል፡፡

ታኀሣሥ 18 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *