የትራፊክ ቅጣትንና የፖርኪንግ ክፍያን ያዘምናል የተባለለት ሶፍትዌር ይፋ ሆነ

የአ/አ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን በኢንፍራቴክ የሶፍትዌር አበልፃጊ ድርጅት የተሠራ የትራንፖርት ችግሮችን የሚቀርፍና ለህብረተሰቡ ቀልጣፋ፣ ጊዜንና ገንዘብን የሚቆጥብ አዲስ ሶፍትዌር ዛሬ ይፋ አድርጓል።

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ክበበው ሚደቅሳ ፤ሶፍትዌሩ የትራፊክ ቅጣትንና የፖርኪንግ ክፍያን የሚያዘምን ነው ብለዋል።

አቶ ክበበው በኢትዮጵያ ብሎም በከተማዋ የሚደረገውን እንቅስቃሴ በቴክኖሎጂ የማስደገፍ ጥረትን አንድ እርምጃ ከፍ ያደርጋልም ሲሉ ተናግረዋል።

ኢንፍራቴክ የሶፍትዌር አበልፃጊ ድርጅት በተለያዩ ተቋማት ያሉ አሰራሮችን በይበልጥ ከማዘመን ባለፈ ተቋማት ለአገልግሎት አቅራቢዎች የሚከፍሉትን የውጭ ምንዛሪ እያስቀረ መሆኑ ተገልጿል።

ድርጅቱ ከሀገር ውስጥ ባለፈም የተለያዩ ሶፍትዌሮችን በማበልፀግ ወደ ውጪ ለመላክ መዘጋጀቱንም አስታውቋል፡፡

ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሚደረገውን ጉዞ በማገዝ ረገድ ትልቁን ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ተጠቁሟል።

ልኡል ወልዴ

ታኀሣሥ 24 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *