አዲሱ የሶሪያ የዉጭ ሚኒስትር ሳኡዲ አረቢያ መግባታቸዉ ተሰማ

የበሽር አል አሳድን አገዛዝ አስወግዶ ስልጣን በያዘው ሃይል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዲሆኑ የተሾሙት ሺባኒ በሳኡዲ የመጀመሪያ የውጭ ሀገር ጉብኝታቸውን ነው እያደረጉ የሚገኙት።

ደማስቆ ከሪያድ ጋር ትብብሯን ለማጠናከር ያላትን ፍላጎት ያመላክታል ተብሏል ፡፡

አል ሻራ ሳኡዲ አረቢያ በሶሪያ ቀጣይ እጣፈንታ ትልቅ ድርሻ ይኖራታል ብለዋል፡፡

ሶሪያ ባለፈው አመት ዳግም ወደ አረብ ሊግ እንድትመለስ የሳኡዲ አረቢያ ሚና ከፍተኛ እንደነበር ይታወሳል።

ልዑክ በሳኡዲ ቆይታው የሪያድ እና ደማስቆን ትብብር በሚያሳድጉ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል ሲል አልጄዚራ ዘግቧል፡፡

አባቱ መረቀ

ታኀሣሥ 24 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *