ለመጀመሪያ ጊዜ የጥምቀት ኤክስፖ የንግድ ትርኢትና ባዛር ሊካሄድ ነው።

በመዲናችን አዲስ አበባ የመጀመሪያ የሆነው የጥምቀት ኤክስፖ የንግድ ትርኢትና ባዛር በኤግዚቢሽን ማዕከል ሊካሄድ ነው።

የጥምቀት ተዋህዶ ኤክስፖ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተክህነት በተሰጠ እውቅና እና ፍቃድ መሰረት የአዲስ ዓመት፣የመስቀል ፣የገና፣የጥምቀት፣የፋሲካና የዳግመ ትንሳዔ ሀይማኖታዊ ስነስርዓቱን በጠበቀ መልኩ ይደረጋል ተብሏል።

የማርኮናል ኤቨንትና የዚህ የጥምቀት ኤክስፖ ዋና አዘጋጅ አቶ ኤፍሬም አደፍረስ ፤ይህ ኤክስፖ  ዜጎችን በአንድ ማዕቀፍ በማድረግ በሰከነ መንፈሳዊ ስነ- ምግባር ባለውና በታዓማኝነት ይከናወናል ብለዋል።

ምርትና ልዩ ልዩ  አገልግሎቶች የሚቀርብበት  እንዲሁም ለማህበረሰቦች በየ ደረጃው የስራ እድል የመፍጠርና የሀገር ገጽታ የሆነውን በዓላቶቻችንን ለቱሪስት መስህብ በሚሆን ደረጃ በመስራት አለም አቀፍ ግንኙነትን መፍጠር ዓላማ ያደረገ መሆኑ አቶ ኤፍሬም ተናግረዋል፡፡

“አብሮነት ለእድገት “በሚል መሪ ቃል የሚሰናዳው ይህ «ጥምቀት ኤክስፖ የንግድ ትርኢትና ባዛር ከጥር 03 እስከ ጥር 09 ቀን 2017ዓ/ም ለተከታታይ 7 ቀናት በኤግዚቢሽን ማዕከል ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚካሄድ ሰምተናል።

ኤክሰፖው እጅግ አነስተኛ በሆነ የነጋዴዎች መሳተፊያ ዋጋ የቀረበ መሆኑም ተገልጿል ።

በኤክስፖ ከአልኮል መጠጥ ምርቶች ውጪ ያሉ የትኛውም የተለያዩ የማህበረሰብ መገልገያ ቁሳቁሶችንና ነዋየተ ቅዱሳትን በማካተት የህብረተሰቡን የኑሮ  አቅምን ባገናዘበ ዋጋ የሚገኝበት የገበያ አማራጭ ይሆናል ተብሏል ።

በተጨማሪ ያለ ምንም የሀይማኖት ልዩነት የትኛውንም አማኝ በመቀበል የሚያስተናግድ የንግድ ትርኢትና ባዛር መሆኑን አዘጋጆቹ አስተውቀዋል።

እንደ እዘጋጆቹ ገለጻ የጥምቀት ኤክስፖ የንግድ ትርኢትና ባዛር በቀን ከ10ሺህ በላይ ሰዎች እንደሚጎበኙት እንዲሁም ከ150 በላይ ነጋዴዎች እንደሚሳተፉበት ተጠቁሟል ።

ከኤክስፖው ከሚገኘው ገቢ ላይ ተቀናሽ በማድረግ የተለያዩ የመርጃ ማዕከላትንና ገዳማት እንዲሁም ደብራትን ለመደገፍ መታቀዱን አዘጋጆቹ በጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ አስታውቀዋል፡፡

ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *