የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በበዓሉ ዋዜማና በዕለቱ ሊያጋጥም የሚችለውን የኃይል መቆራረጥና መዋዥቅ ችግር ለመቀነስ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያከናወነ ማሆኑን አስታዉቋል ፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ታየ ለጣቢያችን እንዳሉት በበዓሉ ዋዜማና በዕለቱ የኃይል መቆራረጥና መዋዥቅ ችግር ሳይፈጠር ለተጠቃሚው ለማቅረብ ከተከሰተም በአፋጣኝ የአስቸኳይ ጥገና ስራ ለመስራት በየደረጃው ግብረ-ሃይል በማዋቀርና አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን በማዘጋጀት ወደ ስራ ተገብቷል ብለዋል ።
ግብረ-ሃይሉም በተደጋጋሚ የኃይል መቆራረጥና መዋዠቅ ችግር የሚስተዋልባቸውን መስመሮች በመለየት የቅድመ መከላከል ጥገና ስራዎች እያከናወነ ይገኛል ተብሏል ፡፡
በተጨማሪ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጋር በመቀናጀትና የጋራ ግብረ ሀይል በማዋቀር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በጋራ እየተከናወነ መሆኑ ተገልጿል ፡፡
የቅድመ-ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች ደግሞ በዓሉ ሲደርስ የሚኖረውን አላስፈላጊ እንግልት ለማስቀረት ከወዲሁ የኤሌክትሪክ ኃይል አስቀድመው ካርድ እንዲሞሉ አቶ መላኩ አሳስበዋል ፡፡
ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር ተያይዞ ማንኛውም ቅሬታ፣ ጥቆማና አስተያየት ካለ በ905 ወይም 904 ነፃ የጥሪ ማዕከል በመደወል ማድረስ እንደሚቻል ተነግሮል ፡፡
አቤል እስጢፋኖስ
ታኀሣሥ 28 ቀን 2017 ዓ.ም
