በዚህም ምክንያት በሁለት ወር ውስጥ 6 ሰዎች መሞተቻውን ጣቢያችን ሰምቷል።
ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላ በመድኃኒት እና በግብአት እጥረት ችግሮች ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥርም ወደ 90 መድረሱን ተነግሯል፡፡
በትግራይ የኩላሊት ሕሙማን ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሃፍቶም አባዲ ህሙማኑ በገንዘብ እጥረት ምክንያት የከፋ ችግር ላይ ይገኛሉ ያሉ ሲሆን የመድሀኒት አቅርቦት በቅርቡ ቢኖርም ዋጋው ግን የሚቀመስ አይደለም ብለዋል።
በትግራይ ብቸኛው ዲያሊሲስ ማድረጊያ ቦታ በአይደር ሆስፒታል እንደሆነ የሚናገሩት ሃላፊው አሁን ላይ ለአንዴ የሚያገልግል አንድ መድኃኒት እስከ 3ሺ 9 መቶ ብር ድረስ እየገዙ እንደሚገኙ ነግረውናል።
በአይደር ሆስፒታል ከ11 በላይ ማሽኖች ከዚህ ቀደም አገልግሎት ይሰጡ እንደበረ አስታውሰው በዚህ ሰዓት ግን አብዛኛው በእድሜ መግፋት ከጥቅም ውጭ እንደሆኑም ነግረውናል፡፡
አሁን ላይ ከ 40 እስከ 46 የሚጠጉ ህሙማን በአይደር ህክምናቸውን እየወሰዱ እንደሚገኙ ጣቢያችን ሰምቷል።
ለአለም አሰፋ
ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም
