የሸገር ከተማ አስተዳደር የጥምቀት በአልን ለማክበር በቂ ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ፡፡

የጥምቀት በአል ህዝቡ አደባባይ ወቶ የሚያከብረው በመሆኑ ህብረተሰቡ በሰላም በአሉን አክብሮ እንዲመለስ ለማስቻል የተለያዩ ስራዎች መሰራቱን የሸገር ከተማ አስተዳደር የአስተዳደር እና ፀጥታ ፅህፈት ቤት ምክትል ሀላፊ አቶ ደሳለኝ ስዩም ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ እቅድ አዘጋጅቶ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግስት ሀላፊዎች ፣የፀጥታ አካላት ፣ በየቤተክርስቲያኑ ያሉ አስተዳዳሪዎች ፣ የስብከተ ወንጌል ሀላፊዎች፣ ቀሳውስት እና ዲያቆናት እንዲሁም ወጣቶችን አሰባስቦ በማወያየት አስፈላጊውን ድጋፍ የማድረግ ስራ መስራታቸውን አንስተዋል፡፡

ከበአሉ ጋር ተያይዞ ስጋት ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን የመለየት ስራዎች መከናዎናቸውንም ጠቅሰዋል፡፡

በአሉ ከሚከበርበት እለት ጀምሮ በቂ የፀጥታ አካላት ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውንም ነግረውናል፡፡

ትልቁ እና ዋናው ስራ ግን ህዝቡ እራሱ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ሰፊ ስራ መሰራቱ ነው ብለዋል፡፡

የበአሉ ባለቤት ህብረተሰቡ በመሆኑ የፀጥታውን ሁኔታ ሊያደፈርሱ የሚችሉ እንቅስቃሴዎችን በሚያስተውልበት ወቅት አቅራቢያው ላለ የፀጥታ አካል ማሳወቅ እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

ህዝቡ በዚህ በአል አከባበር ላይ ሰላም ከማስፈን አንፃር አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያርግ የሚል አስተያታቸውንም ሰተዋል፡፡

ሐመረ ፍሬው

ጥር 8 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *