የጤናማ እናትነት ወር በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ38ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ19ኛ ጊዜ በመዲናዋ ደግሞ ለ11ኛ “ጥራቱን የጠበቀ የምጥና የወሊድ እንክብካቤ ለሁሉም እናት፣ ለጤናማ እናትነት”በሚል መሪ ሃሳብ እየተከበረ ይገኛል።
የዚህ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ዋና አላማ የእናቶችን ሞት ለመከላከል እና ጥንቅቃቄ ለመፍጠር ያለመ መሆኑ ተሰምቷል።
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ ፣በወሊድ ጊዜ እናቶች እስከ ሞት የሚደርስ ከፍተኛ ችግር እንደሚገጥማቸው ጠቅሰው፤ የእናቶች እና ለጨቅላ ህፃናት ጤና አገልግሎት ተደራሽነት ላይ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝም አንስተዋል ።
ሚኒስትሯ በዚህ ወር ከዚህ ቀደም ከምናድረገው በተሻለ የጤና ተቋማትን ወደ ማህበረሰቡ በስፋት ቅርብ የማድረግ ስራ እንደሚሰሩም ተናግረዋል።
ችግሮቹን ለመቅረፍና ግንዛቤ ለመፍጠር በየዓመቱ በጥር ወር የጤናማ እናትነት ወር የሚከበር መሆኑንም አስታውሰዋል ።
የቅደመ ወሊድ ፣ የወሊድ እና የድህረ ወልድ ክትትል ስራ ውጤታማ ለማድረግ በቂ የጤና ባለሞያዎችን በመፍጠር ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የማሰልጠን ስራ እየተሰራ መሆኑም ተነስቷል።
ለዓለም አሰፋ
ጥር 8 ቀን 2017 ዓ.ም
