ለኢንሹራንስ አገልግሎቶች የሚፈጸም ክፍያን በዲጂታል መንገድ ለማድረግ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እና አዋሽ ኢንሹራንስ ትብብር መፈጸማቸዉ ተገለጸ፡፡

ሳፋሪኮም ኤም-ፔሳ ከአዋሽ ኢንሹራንስ ጋር የፈጸመዉ ትብብር፤ የአዋሽ ኢንሹራንስ ደንበኞች ከኢንሹራንስ ጋር ለተገናኙ አገልግሎቶች የሚከፈል ክፍያን ደህንነቱ በተጠበቀ እንዲሁም ምቹ በሆነ መንገድ በኤም-ፔሳ የዲጂታል የክፍያ አገልግሎት በኩል እንዲፈጽሙ የሚያስችል ነዉ ተብሏል፡፡

ሁለቱ ተቋማት በገቡት ትብብር መሰረት፤ የአዋሽ ኢንሹራንስ ደንበኞች ፕሪሚየም ክፍያዎችን እንዲሁም ሌሎች ከኢንሹራንስ ጋር የተገናኙ ክፍያዎችን ቀጥታ በኤም-ፔሳ እንዲፈጽሙ ያስችላቸዋል፡፡

የዲጂታሉ ዘመን ነገሮችን በተቀላጠፈ ሁኔታ የሚያቀርብ በመሆኑ ፤ የኤም-ፔሳ የሞባይል የክፍያ አማራጭን በመጠቀም የኢንሹራንስ አገልግሎቶች ሁሉም ጋር ተደራሽ እንዲሆኑ እየሰራ መሆኑን ሳፋሪኮም አስታዉቋል፡፡

ይህ ትብብር፤ ሳፋሪኮም የዲጂታል የክፍያ አገልግሎቶችን በመላዉ ኢትዮጵያ ለማዳረስ ያለዉን ዕቅድ የሚደግፍ መሆኑም ተገልጿል፡፡

እንደ አዋሽ ኢንሹራንስ ያሉ አገር በቀል ከሆኑ ተቋማት ጋር በትብብር መስራቱ፤ ለአገር ዉስጥ ተጠቃሚዎች እና የቢዝነስ ተቋማት ምቹ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የክፍያ አማራጮችን በማቅረብ ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚዉ በስፋት እንዲገቡ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን ኩባንያዉ አስታዉቋል፡፡

እስከዳር ግርማ

ጥር 9 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *