በተወሰነ መልኩ ግን በሁለቱ ክልሎቸ የሰዎች እና የሸቀጦች እንቅስቀሴ የሚያስተጓጉሉ አካላት መኖራቸውም ተነስቷል፡፡
የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ደ/ር ለገሰ ቱሉ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም መንግሥት በመላ ሀገሪቱ ሰላም እና መረጋጋት ለማስፈን ሢሠራ መቆየቱን ገልጸዋል ይሀ በበዙ መሳካቱን ገልጸዋል፡፡
ደ/ር ለገሰ፤ ነፍጥ ያነሱ ኀይሎች ለንግግር በር እንዲከፍቱ በመደረጉ የታጠቁ ኀይሎች ወደ ንግግር እንዲመለሱ ማድረግ ማቻሉንም አንስተዋል፡፡
በተያያዘም ደ/ር ለገሰ በአማራ ክልል የታጠቁ ኀይሎችም ለውይይት ቅድሚያ ሰጥተው ወደ ተሃድሶ ማዕከል እየገቡ መሆኑን አንስተው በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል በተሠራው ሰላምን የማስፈን ሥራ ለውጦች መምጣታቸውንም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
መንግሥት አሁንም የሰላም አማራጭን መከተል ላይ ቅድሚያ እንደሚሰጥ ያነሱት ሚኒስትሩ፤ አሁንም ነፍጥ ያነገቡ አካላት ወደ ሰላማዊ ሂወታቸው ሊመለሱ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
ሚኒሰትሩ በሌላ በኩል በመግለጫቸው ያነሱት የሸቀጦች እና የሰዎች እንቅስቀሰሴዎች አሁንም በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች የመገደብ ሁኔታ እንደሚታዩ አንስተው እሱን ማሻሻል እንደሚገባውም አንስተዋል፡፡
ለዓለም አሰፋ
ጥር 9 ቀን 2017 ዓ.ም
