የነዳጅ ሽያጭ በኩፖን

የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ንግድና ገቢያ ልማት ቢሮ የነዳጅ ሽያጭ በኩፖን እንዲሆን መወሰኑን አስታወቀ

በቢሮው በኩል ለሁሉም ዞን ንግድና ገቢያ ልማት መምሪያ በተሰራጨው ሰልኩላር ደብዳቤ መሰረት ከጥር 30 ጀምሮ ሁሉም የነዳጅ ማደያ ያለባቸው ከተሞች ከጥር 30/2017 ጀምሮ ነዳጅ በኩፖን እንዲሸጥ ትዕዛዝ አስተላልፏል።

የነዳጅ ምርት እጥረቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከመሻሻል ይልቅ እየተባባሰ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ በተለይ የባለ ሁለት እግር ሞተሮች በየቀኑ ተመላልሶ መቅዳት ለኮንትሮባንድ ሽያጭ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ ለችግሩ መባባስ ዋነኛ መንስኤዎች መሆናቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል ብሏል።

በአንዳንድ የክልሉ ከተሞች የኩፖን ሥርዓት በመዘርጋቱ ሥርጭት ላይ ያለውን የቤንዚን ምርት በአግባቡ ማሰራጨት መቻሉንና ለክትትልም ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ማስተዋሉን ነው በደብዳቤው የጠቀሰው።

በመሆኑም የነዳጅ ማደያ ያለባቸው ከተሞች ከጥር 30/2017 ዓ.ም ጀምሮ የትኛውም ተሽከርካሪ በኩፖን ብቻ እንዲስተናገድ እና ታርጋ የሌላቸው ተሽከርካሪዎች ሀጋዊ የተሽከርካሪ ሠሌዳ እስኪያወጡ ድረስ የግልም ሆነ የመንግስት ተሽከርካሪዎች እንዳይስተናገዱ ሲል በደብዳቤው ጠቅሷል።

ጥር 13 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *