ወ/ሮ ስመኝ ዉቤ የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ዋና ዳይሬክተር ሆነዉ ተሾሙ።

6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ተካሄዷል ።

በዚህም ምክር ቤቱ ቤለዉ ስልጣን እና ሀላፊነት መሰረት የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም የእጩዎች ሲመለምል ቆይቷል።

ለዋና ዳይሬክተርነት በእጩነት ከቀረቡ 60 ግለሰቦች የቀረቡ ሲሆን በምክትል ዋና ዳይሬክተርነት 200 እንዲሁም በዘርፍ እምባ ጠባቂ 85 ግለሰቦች መቅረባቸዉ ተገልፆል።

ከቀረቡት እጩዎች ዉስጥ ወ/ሮ ስመኝ ዉቤ በቀጣይ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተርነት እንዲመሩ ሹመት ተሰጥቷቸዋል።

የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም በምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር የኔነህ ስመኝ እንዲሁም የዘርፍ እምባ ጠባቂ አቶ አባይነህ ኦዳቶ ሆነዉ ተመርጠዋል።

የተቋሙ የእጩነት መስፈርት ከየትኛዉም የፖለቲካ ፓርቲ ነፃ መሆን መሆን እንደሚገባቸዉ ቢቀመጥም እጩዎች የስራ ልምዳቸዉ ሲታይ በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ከፍተኛ አመራር ቦታ የነበሩ መሆን ከምክር ቤት አባል ጥያቄ ተነስቶበታል።

ምክር ቤቱ ባለዉ ሀላፊነት እና ስልጣን የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ የዋና ዳይሬክተርነት÷ የምክትል ዋና ዳይሬክተርነት÷ የዘርፍ እምቤ ጠባቂ ተቋም ሹመት በሙሉ ድምፅ ፀድቋል።

ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *