ለኢንዱስትሪ ማቋቋሚያ የሚሆን ቦታን ባለሃብቶች እንጂ መንግስት እዚህ እዛ ማለት አይችልም ሲሉ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚንስትሩ አቶ መላኩ አለበል ተናግረዋል፡፡
አቶ መላኩ ይህን ያሉት ከምክር ቤት አባላት የኢንዱስትሪዎች አተካከል ፍታዊ አይደለም በሚል ለተነሳላቸው ጥያቄ ነው፡፡
‹‹ባለሃብቱ ገበያን መሰረት አድርጎ፤የሰዉ ሃይልን መሰረት አድርጎ፤ጥሬ እቃን መሰረት አድርጎ በሌላም መልኩ ደግሞ ባለሃብቱ በፍቃዱ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እዚህ ቦታ ላይ ማቋቋም እፈልጋለሁ›› ሲል ያቋቁማል እንጂ መንግስት እዚህ ካልሆነ ብሎ የማስገደድ መብት የለዉም ነዉ ያሉት፡፡
ሚኒስትሩ በዚህ ረገድ የመንግስት ተግባር አማራጮችንና ባለሃብቱ በመረጠዉ ስፍራ ላይ በጥናት ተመርኩዞ ሁኔታዎችን ማመቻቸትና ማማከር ብቻ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ምክር ቤቱ ማንኛዉም በግሉ ባለሃብት የሚቋቋሙ ኢንዱስትሪዎች በባለሃብቱ ዉዴታ እና ይሁንታ የሚፈጸም እንጂ የትኛዉም የፌደራልም ይሁን የክልል ቢሮዎች ፍቃድ ያለመሆኑን እንዲረዳልን እንፈልጋለን ብለዋል፡፡
ልኡል ወልዴ
ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም
