አላስፈላጊ የግብይት   ሰንሰለት  የቆዳ ምርት  ኤክስፖርት ላይ  እንቅፋት ሆኗል ተባለ፡፡

ኢትዮጵያ በቀጠናው  በቆዳ ምርት ኤክስፖርት ቀዳሚ ብትሆንም በዘርፉ ውጤታማ መሆን   አልተቻለም ተባለ፡፡

ለዚህም ለቆዳ የኤክስፖርት ዘርፉ  ውጤታማ አለመሆን   ከፍተኛ የመዋቅር  ችግር በመኖሩ ነዉ ተብሏል ፡፡

ችግሮቹን ለይተናቸዋል የሚሉት   የንግድና ኢንዱስትሪ ሚንስትር አቶ መላኩ አለበል ቀዳሚዉ ከእንስሳት አያያዝንና እርባታ ጋር በተያያዘ  የቆዳን ጥራት የሚቀንሱ ችግሮች መኖራቸዉን አንስተዋል፡፡

ሁለተኛዉ በግብይት ሰንሰለቱ የሚታየው  አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነት ለዘርፉ ዉጤት አልባነት እንደ ምክኒንያትነት አንስተዋል፡፡

ከአመራረት ጋር ተያይዞ በቴክኖሎጂና ዘመናዊ በሆነ አሰራር ዘርፉ ያለመታገዙ  ዘርፍ ለመዳከሙ ከሆኑ ቀዳሚ  ምክንያቶች ዋነኛዎቹ ናቸዉ  ብለዋል፡፡

እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ፖሊሲ ተቀርጾ ወደ ስራ መገባቱን ያብራሩት ሚኒስትሩ  ቢሆንም ግን ችግሩ በአንድ ለሊት የሚፈታ ባለመሆኑ የቅንጅት ስራና ጊዜ እንደሚፈልግ ጠቁመዋል፡፡

በቀጣይም የአምራች ኢንዱስትሪውን መዋቅራዊ ችግሮች በቅንጅት በመፍታት እና የባለድርሻ አካላትን በየደረጃው የበኩላቸውን እንዲወጡ በማድረግ ከፍተኛ ውጤት እንዲመጣ እሰራለን ብለዋል ፡፡

ልኡል ወልዴ

ጥር 16 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *