ሁለተኛው ዙር 2025 አለም አቀፍ የቁርአንና አዛን ወድድር በኢትዮጵያ በሁለት የውድድር መርሃግብር አንደሚካሄድ ተነግሯል፡፡
በውድድሩ ላይ ከ 60 በላይ ሃገራት የተውጣጡ ተወዳዳሪዎች ና የልኡካን ቡድን ተሳታፊዎች እንደሚገኙበት ታዉቋል፡፡
ውድድሩ በሁለት መርሃ ግብር የሚካሄድና የመጀመሪያው ጥር 21 2017 ዓ.ም በኢሊሊ ኢንተርናሺናል ሆቴል ይደረጋል ተብሏል፡፡
የፍፃሜው ውድድር ደግሞ በአዲስ አበባ ስታዲያም ጥር 25 2017 ዓ.ም እንደሚካሄድ የውድድሩ አዘጋጆች አስታውቀዋል ፡፡
ውድድሩን ለመዳኘት ከአስራ አንድ አገራት 11 ዳኞች ይመጣሉ ተብሏል ፡፡
በኢትዮጵያ በኩል ውድድሩን ከማዘጋጀት ባለፈ ሃገር ወክለው የሚወዳደሩ ተሳታፊዎችን ለመምረጥ ከ አንደ አመት በላይ የማጣሪያ ስራ መሰራቱን ሰምተናል፡፡
አቤል እስጢፋኖስ
ጥር 16 ቀን 2017 ዓ.ም
