ብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛውን ጠቅላላ ጉባኤ ሊያካሂድ ነው።

ጉባኤው ከፊታችን ከጥር 23 እስከ 25 2017 ዓ/ ም ይካሄዳል።

2ኛው የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ከጥር 23 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚካሄድ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እና ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አደም ፋራህ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

“ከቃል እስከ ባህል “ የሚል መሪ ቃል የተሰጠው ይህ ጉባኤ ከ 1 ሺ 7 መቶ በላይ ተሳታፊዎች እንደሚገኙበት ተገልፆል።

የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች፣ የውጭ ሀገራት ወዳጅ ፓርቲዎች ተወካዮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚገኙም ተነግሯል።

በአንደኛው የፓርቲው ጉባኤ ቃል የተገቡ ስራዎችን በመገምገም በቀጣይም ፓርቲው የሚፈፅማቸውን እቅዶች፣ ያስቀመጣቸውን አቅጣጫዎች እና ትልልቅ ውሳኔዎችን የሚሳልፍበት ጉባኤ እንደሚካሄድ የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ በዛሬው መግለጫቸው አንስተዋል።

ጉባኤው በዘላቂ ሰላም፥ በጸጥታ ሁኔታ፣ በኑሮ ውድነት፥ ፓርቲውን በሚያጠናክሩ ውሳኔዎች፣ እንዲሁም
የፓርቲ አመራሮች የሚመረጡበትም ይሆናል ብለዋል።

ከ15 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች እንዳሉት ያስታወቀው ብልፅግና ፓርቲ ባለፍት አመታት በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካዊ፣ በማህበራዊ፣ በዲፕሎማሲ፣ በሰላም እና ደህንነት እና በመሰል ሃገራዊ አጀንዳዎች ላይ ስኬታማ እንደነበር አስታውቋል።

የውልሰው ገዝሙ

ጥር 19 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *