ከኮንዶሚኒየም ያነሱ ቤቶችን ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የማህረሰብ ክፍሎች ለማቅረብ እየተሰራ ነው ተባለ

የቤቶች ልማት ኮርፖሮሽን መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀጋዬ፤ የቤት ችግርን ለመፍታት የተለያዩ ስራዎች መሰራታቸውን የገለፁ ሲሆን በተለይም በከተሞች ያለውን የቤት እጥረት ለመቅረፍ ከኮንዶሚኒየም ያነሱ ቤቶች ለመስራት መታቀዱን አንስተዋል።

ከዚህ ቀደም በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት በተነሳው ኮንዶሚኒየም ዝቅተኛው የቤት ደረጃ መሆን የለበትም የሚለውን ሀሳብ በመያዝ ከኮንዶሚኒየም ያነሱ እንደ ዶርምተሪ አይነት ቤቶችን በብዛት ለመገንባት ጥናቶች መኳሄዳቸውን አንስተዋል።

የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በ6 ወር ውስጥ 20 ሺ 7 መቶ 54 ቤቶች በመንግስት ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ባልሆ መንገድ መገንባታቸውን በመግለፅ በቤት ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ጥሩ መሆናቸውን አመላካች ነው ብለዋል።

አቶ ፀጋዬ ከኮንዶሚኒየም ያነሱት ቤቶች ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው እና ለመንግስት ሰራተኞች በቀላሉ በኪራይ የሚያገኙበትን መንገድ ነው በጥናት ተቀርፆ እየተሰራ ነውም ብለዋል።

በሀገሪቱ 35 በመቶ የሚሆኑት ቤቶች የሚገነቡት በመኖሪያ ህብረት ስራ ማህበራት ነው የሚሉት መሪ ስራ አስፈፃሚው፤ በክልሎች ደግሞ ይህ ስራ በስፋት እየተሰራበት መሆኑን አንስተዋል።

ኮርፖሬሽኑ ቤቶችን እንደልብ ለመገንባት የመሬት እና የፋይናንስ አቅርቦት ችግር አንዱ እና ዋነኛው መሆኑንም ገልፀዋል።

በዚህም እንደ መፍትሄ የቀረበው በቅርቡ በሚወጣው የሊዝ አዋጅ ላይ ከሚቀርበው መሬት በአስገዳጅ ሁኔታ 30 በመቶውን ለቤት ልማት እንዲውል ማድረግ መሆኑንም አቶ ፀጋዬ አስረድተዋል።

ለዓለም አሰፋ

ጥር 19 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *