የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ስሙ ሰንጋ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መሆኑን ፖሊስ አሳውቋል፡፡
የልደታ ክ/ከተማ ፖሊስ አደረኩት ባለው ብርቱ ክትትል በህገ-ወጥ መንገድ በአንድ ኮንቴነር ውስጥ በጀሪካን ተሸሽጎ የነበረ 2ሺህ 360 ሊትር ቤንዚል ከሁለት ግለሰቦች ጋር በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ ገልጻል፡፡
ግለሰቦቹ መንግስት ያወጣውን የነዳጅ መመሪያ በመተላለፍ የሀገር ሀብት የሆነውን ነዳጅ በህገ-ወጥ መንገድ ሊሸጡ ሲሉ መያዛቸውን የፖሊስ የምርመራ መዝገብ ያስረዳል።
ህብረተሰቡ በመሰል የወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ ግለሰቦችን ሲመለከት ለፖሊስ ጥቆማ እንዲሰጥም የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
ጥር 19 ቀን 2017 ዓ.ም
